ብርሃኑ አንተነህ እባላለሁ። በትምህርት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ (ኢኮኖሚስት) ነገር ግን በዓለም ዙሪያ በየዕለቱ የምታዘባቸው ለሰው ልጅ የአሁን እና የወደፊት የጋራ ዕጣ ፋንታ ጠንቅ የሆኑ ሁኔታወች እና ተጓዳኝ አድራጎቶች በእጂግ የሚያሳስቡኝ ተራ ግለሰብ ነኝ። ባጭሩ ዓለም ሠላም የሰፈነባት እና ሁሉም የዓለም ሕብረተሰብ አባል ካለሥጋት የደስታ ተቋዳሽ የሚሆንባት ፍትሀዊ እንድትሆን እመኛለሁ። የድሕረገጼ (justice4allandall4justice.com) እና የዩትዩብ የቴሌቪዥን መስኮቴ ስያሜ ከዚሁ ዕምነቴ የመነጨ ነው።