ፋኖ ማን ነው

Share This

ሰሞኑን ስለፋኖ ብዙ ንትርክ እሰማለሁ። ብዙወች በጥሞና ላዳመጣቸው የፋኖን ምንነት ካለማወቅ እንደመነጩ ያስታውቃሉ። ከፋኖ አቅጣጫ በተለይ መንግሥት ጣቱን ቀሰረብን ብለው በማመናቸው እራሳቸውን ግልጽ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት ፋኖን ለመግለጽ ሞክረዋል። በቅርቡ በባሕር ዳር እና በምሥራቅ ጎጃም በሥልጠና ላይ የነበሩ የፋኖ አባሎች ከመንግሥት ጋር በወገኑ ኃይሎች መበተናቸው ሲሰማ የፋኖወች ሥጋት ምክንያታዊ ይመስላል። እንዲያውም ባለፉት ሁለት ቀናት ሾልኮ የወጣ የተባለ የመንግሥት ሠነድ የተወሰነ የፋኖን ክፍል ከአሸባሪወች ዘርፍ እንደመደበ ይወራል። ፋኖ ያልሆኑ አንዳንድ ግለሰቦችም ከቅንነት በመነሳት የፋኖን አገላልጽ የሚያጠናክሩ ሃሳቦች ይሰነዝራሉ። ሆኖም እነዚህ ሙከራወች በተናጠልም ሆነ በጥቅል ፋኖን በሙሉ ስለማይገልጹ የጎደለችዋን ለመሙላት ይችን አጭር ጽሑፍ ይዠ ብቅ አልኩ። የጽሑፏ ዓላማ መግባባትን በመፍጠር አስፈላጊ ወደ አልሆነ አዝማሚያ የመሄድ ዕድልን ለማመናመን ነው።

Click here to download a file

Leave a Comment