የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ በተለያዩ የኃይል ዘርፎች ተደራጅተው አገልግሎት ለሚሠጡ አባሎች ዕውቅና እና ምሥጋና በሠጠበት ወቅት የነበሩ ትዕይንቶች በዚህ ቪዲዮ አማካኝነት ቀርበዋል። በጣም የሚደንቁ እና ደስ የሚሉ አድረጃጀቶች ናቸው። ችግሩ እነዚህ የፈረጠመ የችግር መከላካያ ክንድ ስለሆኑ ለምን ይህን ያህል ዝግጅት አስፈለገ የሚል ጥያቄ ያስነሳሉ። መልሱ ደግሞ በመጀመሪያ የጸጥታ ሥጋት መኖሩ ሲሆን የሥጋቱ መነሻ የፖለቲካ መበላሸት እንደ ሆነ ግልጽ ይሆናል። ይህ ታዲያ ጥሩ ዜና አይደለም። የባሰ የሚያሳዝነው ደግሞ መንግሥት የሠላም ሥጋቱን የፖለቲካ ችግሩን በመፍታት በማቃለል ፋንታ ክንዱን ለማፈርጠም መምረጡ ሕዝቡን ምናባትህ ትሆናለህ የሚል የአምባ ገነንነት መልዕክት ያዘለ መሆኑ ነው።