መንግሥቱ “ትግላችን”ን ሲጽፍ እረዕሱ እራሱ ምን ያህል አላዋቂ እንደሆነ ከሚያሳየው በላይ በውስጡ ስለፋኖ ያለውን ማንበብ ወይም በአገልግል በዚህ ቪዲዮ እንደቀረበው ማዳመጥ መንግሥቱ ስለፋኖ ምንም ግንዛቤ እንደሌለው ያሳያል። መንግሥቱ ቅን ምኞት ይኖረው ይሆናል። ነገር ግን ከውትድርና ባሻገር ስለሕብረተሰብ ምንም የማወቅ ሙከራ ያላደረገ ስለሆነ አለማወቁ አይፈረድበትም። አውቃለሁ ብሎ የማያውቀውን ሲዘላብድ ግን ስህተት ነህ ማለት ተገቢ ነው።