ፋኖ ማን ነው
ሰሞኑን ስለፋኖ ብዙ ንትርክ እሰማለሁ። ብዙወች በጥሞና ላዳመጣቸው የፋኖን ምንነት ካለማወቅ እንደመነጩ ያስታውቃሉ። ከፋኖ አቅጣጫ በተለይ መንግሥት ጣቱን ቀሰረብን ብለው በማመናቸው እራሳቸውን ግልጽ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት ፋኖን ለመግለጽ ሞክረዋል። በቅርቡ በባሕር ዳር እና በምሥራቅ ጎጃም በሥልጠና ላይ የነበሩ የፋኖ አባሎች ከመንግሥት ጋር በወገኑ ኃይሎች መበተናቸው ሲሰማ የፋኖወች ሥጋት ምክንያታዊ ይመስላል። እንዲያውም ባለፉት ሁለት ቀናት ሾልኮ …