አድዋ የማን ድል ነው?
እኛ የሰው ልጆች ብዙ የማያወዛግቡ ጉዳዮች ያወዛግቡናል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርት እና የባሕል ሚኒስትር ባለሥልጣን የአድዋ በዓል እንደተለመደው የሚኒልክ ሀውልት በቆመበት ማዕከል እንደማይከበር ማስታውቁን ተከትሎ ሃሳቡን ከሚቃወመው አቅጣጫ ጫጫታው በዝቷል። የጫጫታው ይዘት የድል በዓሉ በተለመደው ማዕከ አለመከበር የበዓሉን ታሪካዊ ምንነት ያሳንሰዋል የሚል ነው። እኔም ስሜቱን እጋራዋለሁ። ስለሆነም ለመላው ዓለም በተለይም ለኢትዮጵያዊያን የበዓሉን ምንነት ለማስገንዘብ የምትከተለውን …